የብል[ፅ]ግና መንገድ ክትባት በዩኒቨርሲቲ...!
Edited by : addiskignit@gmail.com -1/3/2023
ሰሞኑን የብል[ፅ]ግና ካድሬዎች ሲጨንቃቸው ልክ እንደ አባታቸው ኢህአዴግ ሁሉ ተሯሩጠው ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓመታዊ ክትባት ለመስጠት መሽገዋል። የክትባቱ ስም" በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" የሚል ሲሆን የክትባቱ ዋና አስፈፃሚዎች ደግሞ በህዝብ የተጠሉ( የተጣሉ) ካድሬዎች ናቸው። የክትባት ሰነዱ ይዘት 54 slides የያዘ ሲሆን የተለያዩ ጉዳዮችን ለመዳሰስ ሞክሯል። ዓላማውም የ4+ ዓመታት የብል[ፅ]ግና ጉዞን ለ "ምሁራን" ማሰረፅ ነው። በሌላ አነጋገር፣ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጥምቀት የሰነበትን የምሁር ካድሬን በብል[ፅ]ግና ወንጌል አእምሮውን ለማደንበሽ፣ ልቡን ለመስለብ የታለመ ነው። ከክትባት ሰነዱ ውስጥ አስገራሚው ጉዳይ ሁላችንም በጋራ የምናውቀውን ሀቅ በፈጣጣው ገልብጦ የማቅረብ እና ገና ለአቅመ-መንግስትነት ያልደረሰው ስብስብ ተዓምረኛ ስራዎችን እንደፈፀመ ማታቱ ነው። ከነዚህ መካከል፣ "መንግሥት ለህግ ተገዢነቱን አስመስክሯል" ይለናል። እንኳን የህግ የበላይነት ማክበር ማስመሰል ያልቻለ ስብስብ ነው። ሌላ ቦታ ደግሞ ከዘመናዊ ትምህርት አንፃር ትውልድን በ4 ይከፍልና ኢህአዴግ ላይ ይቆማል። እውነታው ግን 4ኛው ዘመን (ኢህአዴግ ቁ. 1) ድ*ቁርናን እንደ ሰደድ እሳት ያስፋፋ ሲሆን የብል[ፅ]ግና ስብስብ ግን በድ*ቁርናችን ፍፁም እንድንኮራ ያደረገን ነው። መቼም ማፈር የሚባል ነገር የለም እኮ። ተአምራቱ ይቀጥላል። ቀውሱ የገጠመን "የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋታችንና የዴሞክራሲ ባህል በማለማመዳችን ነው" ይላሉ። ዴሞክራሲ ከወዴት ነሽ? የፖለቲካ ምህዳር የሰፋው የአንድ ግለሰብ አንባገነን ስርዓት በመስፈኑ ይሆን? ወይስ እኔ ተኝቼ ትርጉሙ ተቀየረ? ጉድ እኮ ነው። ደግሞ የስኬቶች ብዛት Assደማሚ ነው። የኢኮኖሚው ፍልስፍና አገር በቀል ነው😍 እናም ባለ ግዙፍ ምጣኔሀበት ባለቤቶች አደረገን። ከአንድ ወር በታች የወረደው የመንግስት ካዝና፣ የኑሮ እብደት፣ የውጪ ንግድ ማሽቆልቆል እና የኢንቨስትመንት ( FDI) መሞት፣ የብር ገለባ መሆን፣ የMacroeconomy crisis፣ ወዘተ የሚስተዋለው ኬንያ መሆኑ ነው😄 ከሁሉም በላይ የሚደንቀው በዲፕሎማሲው ድል ነስተናል የሚለው ማብራሪያ ነው። በዲጂታል ወያኔ ተበልጦ የከረመ መንግሥት የውጭ ግንኙነትን አዘመንኩ፣ ድል ተቀናጀሁ ሲልህ እንዴት አስችሎህ ቁጭ ብለህ ታዳምጣለህ? ባሻዬ፣ ለፕሮፓጋንዳስ ቢሆን አይከብድም ወይ!? ምሁራንስ ምን ቢበድሉ ነው እንዲህ የጨከንክባቸው!???😎 ኧረ እንዲያውም " መንግሥታችን ጄኖሳይዳል እንደሆነ የተከፈተብን ውንጀላ ቀልብሰናል" ይለሃል። ይሄ በአማርኛ ሲገለፅ፣ አሰቃቂ ወንጀል ዜጎቻችን ላይ ብንፈፅምም ለጊዜው ከተጠያቂነት አምልጠናል( we can get away with our crimes" ማለት ነው። በክትባቱ ሰነድ ላይ ስለ ሁሉም ጉዳይ( ህግ፣ ፖለቲካ፣ እኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ የአገረ-መንግስት ግንባታ፣ ታሪክ፣ ወዘተ) ከዳሰሰ በኋላ መውጫ( መፍትሄ) ላይ ያቀረበው ከ1-4 ችግራችን የአገረ-መንግስት ግንባታ ችግር ነው ይላል። ጎበዝ ምን አለበት ቢያንስ የአገረ-መንግስት(state-building) እና ብሄረ-መንግስት( nation-building) ልዩነት እንኳን በአግባቡ ተረድታችሁ ክትባቱን ብትሞክሩ? የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ብሄረ-መንግስት እንጂ የአገረ-መንግስት አይደለም። ሁለቱ ተመጋጋቢ ቢሆኑም እንዲሁም የአገረ-መንግስት ግንባታ ችግር በመጠኑ ቢኖርም ዋናው ችግራችን የህዝቦች( in plural form) ግንኙነት እና በህዝብ እና ገዢዎች መካከል ያለው መስተጋብር ችግር ነው። ቢሆንም እንኳን እንዴት የችግራችን ሁሉ ምንጭ የአገረ-መንግስት ግንባታ ብቻ ይሆናል። የሰነዱ ዝርክርክነት ተዘርዝሮ ስለማያልቅ፣ ወደ ምሁራን ሚና እንመለስ። ምሁራን በዚህ ሂደት ውስጥ ሚናቸው ምን እንደነበር እና ችግሩን ለመቅረፍ ምን ማድረግን እንዳለባቸው የተቀመጠ ጥናት የለም። የተገለፀው ብቸኛው ጉዳይ "ከብሄርና ጥቅመኝነት ወጥቶ ለአገር አንድነት ማሰብ" የሚለው ነው። ዋናው ጥያቄ ግን ምሁራን የአእምሮአቸውን ጭማቂ ለትውልድ እንዳያደርሱ ያደረገው መዋቅራዊ ችግር:- የካድሬ ጣልቃ ገብነት፣ የተቋም ነፃነት እጦት፣ የምሁራን ክብር ያለመኖር፣ የደሞዝ እና ሌላ ጥቅማጥቅሞች ጉዳይ፣ የምርምር ባህል ያለመዳበር፣ የትምህርት ተቋማትና በኢንደስትሪ እና ምማህበረሰብ መካከል ያለው ግንኙነት፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ብሄርተኝነት መጣበቅ( quest for higher education as a form of self-determination)፣ ወዘተ ጥያቄዎች የት ሄዱ? የመምህራን የቅርብ ጊዜ ጥያቆዎችስ ምን ላይ ደረሱ!??? ሲጠቃለል፣ የክትባቱ ብቸኛው ዓላማ የመምህራንን ጥያቄ ማዳፈን፣ የኢህአዴግን መጥፎና የከሰረ ፕሮጀክት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደ አዲስ ማስፋፋት እና አገር የገጠማትን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ከአቅመ-ቢስ የብል[ፅ]ግና ስብስብ ላይ ወስዶ ለሌላ አካል ለማሸከም መሞከር ነው። ችግሩ ግን ለአጭር ጊዜም ቢሆን ከጥቅሙ ጉዳቱ እጅግ ያመዝናል፤ ምክንያቱም ይሄን መንገድ አባታቸው ኢህአዴግ ቁ. ፩. ሞክሮት ፈተናውን ወድቋል። የብል[ፅ]ግና ወንጌል ሰባኪያን ሆይ፣ ለዛሬ አልተሳካም ሌላ ነገር ሞክሩ። መምህራን ሆይ፣ ከጥያቄያችሁ ዓይናችሁን ለደቂቃም አታንሱ!
test