የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጸጥታ ኃይሎች በዓሉን ለማክበር በተገኙ ታዳሚዎች ላይ በፈጸሙት ድብደባና በተኮሱት ጥይትና አስለቃሽ ጭስ በርካቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል በማለት ከሷል
Edited by : addiskignit@gmail.com -3/3/2023
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ትናንት በምንሊክ አደባባይ በተከናወነው የታላቁ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ወቅት በበዓሉ ታዳሚዎች ላይ በወሰዱት "አላስፈላጊ" እና ከመጠን ያለፈ" የኃይል ርምጃ አንድ ሰው ሞቷል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ፣ ጸጥታ ኃይሎች አረጋዊያንና ሕጻናትን ጨምሮ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በዓሉን ለማክበር በተገኙ ታዳሚዎች ላይ በፈጸሙት ድብደባና በተኮሱት ጥይትና አስለቃሽ ጭስ በርካቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል በማለት ከሷል። ጸጥታ ኃይሎች ዳግማዊ ምንሊክ አደባባይ በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የታደሙ ምዕመናንን ጭምር በኃይል በትነዋል ብሏል።
test