
ቶምን ደብቄ ያገኘሁት ይመሥለኛል።
ይህቺ ጠባቧ የሁል ጊዜ ማረፊያችን የሆነችው ካፌ ውስጥ ሁለት ሶስት ሠዎች በእርጋታ መፅሀፍ እያነበቡ እና ቡና እየጠጡ ተቀምጠዋል። እንደኔና እንደቶም ደግሞ ምሳ ሰአቱን ኮራሳ ኬክ እንደጓደኛ፣ እንደአለቃ ይሁን እንደወንድምና እህት ወይ ደግሞ እንደልቦቻችን መውደድ ብቻ በነፃነት እየተጎራረሰ ለማውራት ደንበኛ ሊሆን የሚመጣ ይመሥለኛል።
what is your philosophy ?
አለኝ ቶም ገብተን ከተቀመጥንበት አንዱ ጥግ ላይ የተፃፈውን የግድግዳ ላይ ፅሁፍ እያነበበ።
"አንተን ማፍቀር አልኩት ፈጥኜ። ቀይ ፊቱ ቲማቲም ሲመስል ከአፌ ምን እንደወጣ መለስ ብዬ ማሠብ ጀመርኩ። ቶም አለቃዬ ነዋ! የኔ ብቻ ሳይሆን የሱፐርቫይዘሮቹ ጠቅላላ አለቃ! ግን ደግነቱና ትህትናው ስለሚበልጥ እንደአለቃ የሚያርቀው የለም።
አቅፎ በሞቀ ፍቅር ያሻሻል። ጥሩነቱን ታክኬ አፈቀርኩት።
ቀስ እያልኩኝ ውስጤ አሠረፅኩት። አሁን ቶም ውስጤ ተንሰራፍቷል።
Day time friends,
Night time lover እያለ መዝፈን ጀመረ። ሙዚቃው where they go what they do እያለ ይንቆረቆራል የKenny Rogers ሙዚቃ ሀገረሰብ ስልት ነው። አዝማቹን ደጋግሞ አለው። የኔ ልብ ደግሞ ስራውን ያቆመ እስኪመስለኝ ተናጠ።
"ቀንሽ እንዴት ነበር?" አለኝ አይኑን ከኔ እያሸሸ እና ግድግዳው ላይ እየወረወረ።
ግድግዳው ከጥግ እስከጥግ በጥያቄና መልስ ፅሁፍ ተሞልቷል።
ቆርጬ የያዝኩትን ኮራሳ ኬክ ለመብላትና ለመተው የማመንታት ስሜት ተሰማኝ። ስለብቸኝነት በጥልቀት ማሰብ ጀመርኩ። ሁል ጊዜም ከቶም ጋ ስሆን የብቸኝነቴን ገመድ የበጠስኩ ይመሥለኛል። አብረን ነበር ውሏችን አዛዥና ታዛዥ ሆነን። እንደአህያ መፍጋቴ ሲያበሳጨኝ በየመሀሉ በሆነ አጋጣሚ ወደራሱ እቅፍ ያደርገኝና አይዞን ይለኛል። ወዲያው ልቅቅ ያደርገኝና ካሜራ ላይ ነን ሰዎች ብሎን ወደሌሎቹ ሰራተኞች ይሄዳል። ሲስቅ፣ቁም ነገር ሲያወራም ያምራል. .
🎷🎷
የጊታሩ ድምፅ ጎልቶ ይሠማል። የተፈጠረበትን ስሜት ለመሸሽ ሲሞክር ጭራሽ ተደናበረ። የመደናበር ስሜቱን ለማጥፋት ደግሞ ድምፁን አጉልቶ መዝፈን ጀመረ።
"ቶም አንተ ቶም አልኩት ደጋግሜ ከእንቅልፉ የመቀስቀስ ያህል።
ከት ብሎ ሳቀ። ሁሌም ሳቁ አካባቢውን በደስታ ይሞላዋል።
"ሁሉም ሰው አንድ ጎደሎ ነገር አለው ይላል ፅሁፉ እዛ ጋ ! አየኸው? "አልኩት
"እና. . " አለኝ
የአንተ ጎደሎ ምንድነው? ልልህ ነዋ!
"ሠው ያለጎደሎ ይፈጠራል?"
"ላይፈጠር ይችላል። ለምሳሌ እንዳንተ"
"ማሾፍሽ ነው?"
"ከምሬ ነው አንተ ሁል ጊዜ ቅን ታስባለህ? አልኩት
🎷🎷
Day time friends
እኔን ችላ ብሎ ማንጎራጎሩን ጀመረ።
ስማ አልኩት ደፍሬ ደግሞ ድርቅ ብዬ. . ነፃነት ያስለመደኝ እሱ ነዋ ይሉታዬን ያስጣለኝ። አስተያየት እስክሰጥ እየጠበቀኝ
"ስማ አላልሽም? እየሠማሁ ነው ቀጥይ?" አለኝ። ጎራዳ አይሉት ሰልካካ መሀል የቀረ አፍንጫውን እያሸ። አይኑን ደረቴ ላይ ሰክቷል ። የወንድ ልጅ አይን ቡናማ ሲሆን እወዳለሁ። ንፁህ መሥሎ ይታየኛል። ንፁህ ነገር እወዳለሁ ጅው ብሎ ውስጡ ለመውደቅ እንዲመቸኝ።
" አላጎረስከኝም?"
"ኦ ማይ ጋድ. . " አለኝ እና ከንፈሩን ነከሰ።
ከንፈርን ነክሶ መሳም እወዳለሁ የጊዜ ቁጭቴን የምወጣበት ይመሥለኛል። የጎደለውን የምሞላ የሞላሁትን የምቀንስ ነክሶ መሳም ጣእሙ የተለየ ነው። በቶም ከንፈር ላይ ማሰቤ ገርሞኝ ሳኩና ቶም አልኩት
ከእንቅልፉ እንደባነነ አይነት" ኮፊ ልድገም" አለኝ
የአንተንም ፍልስፍና ንገረኛ!? አልኩት አስከትዬ
" የኔ ፍልስፍና. . . " እያለ ኮፊ ለማምጣት ከመቀመጫው ተነሳ። ኦረዲ የምሳ እረፍታችን አልቋል ።
ከኋላው በአይኔ ተከተልኩት ሁለመናውን እንደአዲስ ኦያጠናሁ።
" የአንቺን ቀጭን ይሁን ብያለሁ እንቅልፍ ይከለክለኛል ስለምትይ" አለኝ በምልክት
ከዚያ ዝም ብለን ተያየን።
know thy self/ራስህን እወቅ/
አይተኸዋል ስለው
"ጥያቄ ላይ ጥያቄ አትደርቺ ፤ የቀደመውን ልመልስ የኔ ፍልስፍና ጥሩ መስራትና ጥሩ መሆን ነው። አውቃለሁ ከአንቺ ፍልስፍና ጋር ቢራራቅም ሰው ማፍቀር ጥሩ ነው። ነጥሎ መውደድ ሲሆን ፍልስፍና መሆኑን እጠራጠራለሁ።
እኔ አለቃ መሆን እንጂ ሰው ለመውደድና ለመወደድ አልበቃም። የደስታ ቦታዬ ስራዬ ብቻ ነው። ቤቴ ለኔ የሀዘን ማማዬ ነው። እናቴን መንከባከብ አለብኝ። እናቴ የብዙ አመት ህመምተኛ ነች። ገርልፍሬንድም የለኝም። አላስበውም። እናቴ ሁሉ ነገሬ ሆናለች ። ሰባ አምስት ፐርሰንቱ የመኖር ጉጉቴ አላማዬና እቅዴ በስትሮክ ስትመታ አብሮ ተመታ እናቴ ውብ ነበረች ባለጎልደን ፀጉር፣ ዘናጭ የቆንጆ መጨረሻ። ባገባ ምኞቴ እናቴን የምትመሥል ሴት ነበር። ግን እሷን የምትመስል የለችም እና መሥሪያቤቴ ብቻ ነው ሳቄ፣ አፌ የሚፈታው ከንፈሬ የሚላቀቀው፣ ማህበራዊ ቦታዬ. . . አየሽ ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው ይላል ጠቢቡ
/Meaningless! Meaningless!”
says the Teacher.
“Utterly meaningless!
Everything is meaningless.”/
"። አለኝ ሳቁን በሀዘን ለውጦ።
ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ያለይሉኝታ ተርገብግቤ አቀፍኩት። ልቤ ግን ከቦታው ተነቃንቋል።