የአፍሪካ ኅብረት ሰላምና ጸጥታ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ከሐመር ጋር መወያየታቸው ታውቋል
Edited by : addiskignit@gmail.com -6/8/2023
አፍሪካ ኅብረት የሰሜን ኢትዮጵያውን ዘላቂ የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር ለመከታተል ያቋቋመውን ተቆጣጣሪ ቡድን የጊዜ ቆይታ እስከ ቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ወር ድረስ ማራዘሙን የአሜሪካ ኢምባሲ አስታውቋል። የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ለኅብረቱ ተቆጣጣሪ ቡድን በመጀመሪያ የሰጠው የጊዜ ቆይታ ስድስት ወር ሲኾን፣ ኾኖም በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሃት ስምምነት የቆይታ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል ይገልጣል። ባለፈው ታኅሳስ የተቋቋመው የኅብረቱ ተቆጣጣሪ ቡድን አባላት፣ የቡድኑ መሪ ኬንያዊው ሜ/ጀኔራል ስቲፈን ራዲና፣ ናይጀሪዊው ኮሎኔል ሩፋይ ኡመር ማይሪጋ እና ደቡብ አፍሪካዊው ኮሎኔል ቴፎ ስኮሌ ናቸው። የቡድኑ ተልዕኮ አፈጻጸም ጥምር ኮሚቴ እስካኹን ሁለት ጊዜ የቡድኑን የሥራ ክንውን ገምግሟል።
test