ኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ በጋምቤላ ክልል ባንድ የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች እንደተገደሉ ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች
Edited by : addiskignit@gmail.com -5/29/2023
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ በጋምቤላ ክልል ባንድ የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ግንቦት 12 ቀን ባደረሱት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች እንደተገደሉ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች። ጥቃቱ 11 ሰዓት ገደማ የተፈጸመው፣ በምዕራብ ጋምቤላ ቤተል ሲኖዶስ አገልግሎት ክልል "ማታራ" በተባለ ቀበሌ ውስጥ መኾኑን መግለጫው አመልክቷል። ከ2 ሺህ 700 በላይ የመንፈሳዊ ጉባዔው ተሳታፊ ወጣት ሴቶች፣ እናቶችና ሕጻናት መንፈሳዊ የዕለቱን መርሃ ግብር አጠናቀው ለእራት በተቀመጡበት ወቅት፣ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሕጻናትን አፍነው ለመውሰድ በሞሩበት ወቅት፣ ተኩስ እንደከፈቱ ቤተክርስቲያኗ ጨምራ ገልጣለች። ከተገደሉት መካከል አንዲት ሕጻን እንደምትገኝበትና፣ በጥቃቱ የቆሰሉ በርካታ ምዕመናን ጋምቤላ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና ላይ እንደኾኑም በመግለጫው ላይ ተገልጧል።
test