የኢትዮጵያ ማኀበር በቶሮንቶና አካባቢው ከማኀበሩ የአደጋ መከላከል ዝግጁነት ኮሚቴ ጋር በመተባበር የዓመቱን የመዝጊያ ፓርቲ ጋብዟችሁአል
Edited by : addiskignit@gmail.com -12/29/2022
ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የተለያዩ እንግዶችን በመጋበዝ በኮሚኒቲው አባላት መሀከል ቅርርብ እንዲፈጠር የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ሲጥር የነበረው የኢትዮጵያ ማኀበር በቶሮንቶና አካባቢው እነሆ የ2ዐ22 ዓመት የመዝጊያ የብራንች ፓርቲ የፊታችን ቅዳሜ ዲሴምበር 31 ከ 11am እስከ 2pm አዘጋጅቶ እንድትገኙ ጋብዟችሁአል፡፡ በዕለቱ እንደተለመደው የተለያዩ እንግዶች የሚገኙና የልምድ ልውውጥ የሚደረግ ሲሆን የትኬት እጣ የቡና ስነስርአት እና የተለያዩ የጭውውትና የኔትወርኪንግ ተግባራትም ይኖራሉ ተብሏል፡፡ ቅዳሜ ዲሴምበር 31 ከ11am ጀምሮ ቀጠሯችሁን ከ195ዐ ዳንፎርዝ አቬኑ አድርጉ፡፡
test