የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግሥት በ15 ቀናት ውስጥ በድርጊቱ እጃቸው ያለበትን ባለሥልጣናት ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቃለች
Edited by : addiskignit@gmail.com -3/3/2023
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ትናንት ምንሊክ አደባባይ ወደሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ሁለት ጊዜ በተኮሱት አስለቃሽ ጭስ አንድ ምዕመን በጭስ ታፍነው ሕይወታቸው አልፏል ስትል ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ገልጣለች። በድርጊቱ ካህናትና ምዕመናን ለአካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት መዳረጋቸውንና ከ15 ያላነሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደገቡ የቤተክርስቲያኗ ገልጣለች። መንግሥት ትናንት ባወጣው መግለጫ ችግሩን ከሌሎች አካላት ላይ ማላከኩን እንደማትቀበለው የገለጸችው ቤተክርስቲያኗ፣ "እጅግ አሳዛኙ" ድርጊት "የመንግሥት እውቅና ያለው" እና "በዝምታና በሐዘን ብቻ የምታልፈው እንደማይሆን" አስታውቃለች። መንግሥት በ15 ቀናት ውስጥ በድርጊቱ እጃቸው ያለበትን ባለሥልጣናት ለሕግ እንዲያቀርብም ቤተክርስቲያኗ ጠይቃለች።
test