የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በፕሬዝዳንት ዢ ፑንግ ግብዣ በመጭው ዕሁድ ቻይናን ይጎበኛሉ
Edited by : addiskignit@gmail.com -5/12/2023
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በፕሬዝዳንት ዢ ፑንግ ግብዣ በመጭው ዕሁድ ቻይናን እንደሚጎበኙ የቻይናው ሲጂቲኤን ዘግቧል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ፕሬዝዳንት ዢ ፒንግ፣ የኹለቱን አገራት ግንኙነት ወደ "ስትራተጂካዊ አጋርነት" ለማሳደግ ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ማስታወሳቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ቻይናባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሾመቻቸው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኳ ኤርትራን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
test