ለምረቃቸው በተሰባሰቡ አብሮ አደጎች መሃከል ድንገቴ የጋብቻ በአላቸውን ያከበሩት ወላጆች!
Edited by : Gezahegn Mekonnen Demissie -8/13/2025

ለአዲስ ቅኝት ሚዲያ ዘገባውን ያደረሰን ጋሽ አቤል አድማሱ ነው።
የተከበራችሁና የተወደዳችሁ በቶሮንቶና በአካባቢው ነዋሪ የሆናችሁ ኢትዮዽያውያንና ኤርትራውያን ወገኖቻችን እንደምን ሰንብታችኋል !
ባለፈው July 19/2025
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የሆኑት የቅርብ ወዳጆቻችን የልጃቸውን የዩኒቨርስቲ ምርቃት ምክንያት በማድረግ ባደረጉልን ጥሪ መሰረት ከልጄ ሚካኤል ጋር ሄደን የበዐሉ ታዳሚ ሆነን እጅግ የሚያስደስት ቤተሰባዊ መልካም ግዜ አሳልፈን ተመልሰናል።
በዐሉን በይበልጥ አስደሳችና ታሪካዊ የሚያደርገውና መዘገብ አለበት ብዬ ያመንኩበት በቂ ምክንያት በዚሁ በቶሮንቶ ከተማ ተወልደው ያደጉ በተመሳሳይ እድሜ ክልል የሚገኙና አብዛኛዎቹ በመንበረብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠምቀው አብረው እየዘመሩ ያደጉ በሰንበትና በየክብረ በዐላቱ ቤተክርስቲያኗን ያደመቁ ውድ ልጆቻችን አድገው ለቁምነገር በቅተው አብረው እንደዚህ ያለ በዐል ሲያከብሩ መመልከትን የመሰለ አስደሳች ክስተት የበለጠ ይኖራል ብዬ አልገምትም።
በተለይ ከዚህ ፅሁፍ ጋር አያይዤ የላኩት የግሩፕ ፎቶ እንደሚያሳየው በአንድ ከተማ ተወልደው በአንዲት ቤተክርስቲያን ተጠምቀው አድገው ለቁምነገር የበቁ ወጣቶችን ነው።
በዚህ የተቀደሰ እለት ልጆቻችን ያደጉት በአካል ብቻ ሳይሆን በአይምሮና በቁምነገር መሆኑን የሚያሳይ አስደሳች ነገር የተፈጠረው የምርቃቱ በዐል መገባደጃ ላይ የእለቱ ተመራቂ ወጣት ወይዘሪት ሳራ ጌትነት የተወዳጅ አባቷን የአቶ ጌትነት አበጀንና የእናቷን ወይዘሮ ታደለች አየለን የ30ኛ አመት የጋብቻ በዐል ምክንያት በማድረግ በድብቅ ያዘጋጀቺውን ዝግጅት ይፋ አድርጋ በወርቅ ካባና በጣፋጭ ኬክ የታጀበ ግሩም ሰርፕራይዝ አድርጋ የራሷን የትምህርት ምርቃት በዐል ምክንያት በማደግ የተሰበሰበውን ወዳጅ ዘመድ ሁሉ የደስታ እንባ ያራጨ አስደሳች ሰርግ የመሰለ በዐል እንድናሳልፍ ምክንያት ሆና በመገኘቷ እጅግ አድርገን እናመሰግናታለን።
ልጃችንን ሳራን እግዚአብሔር በህይውቷ ሁሉ የበረከት የጤናና የደስታ የስኬት ዘመን ያድርግላት።
ውድ ወዳጆቻችን ወይዘሮ ታደለችና አቶ ጌትነት ላለፉት ረዥም አመታት በቶሮንቶ የኖሩ ከመሆናቸውም በላይ በቤተክርስቲያና በእድር ከኢትዮጵያውያን ህብረተሰብ ጋር ተባብረው በፍቅር በሰላም የኖሩ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ቤተሰቦች በመሆናቸው እኛም ወዳጆቻቸው እንኳን ለ30ኛ አመት የጋብቻ ቀን እደረሳችሁ እንላለን
ለሁሉም እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን !!
አቤል አድማሱ!
ነሐሴ-2025
test