የሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ወርሃዊ የመታሰቢያ ፕሮግራም ነገ ቅዳሜ በደማቅ ዝግጅት ይጠናቀቃል!!
Edited by : addiskignit@gmail.com -3/3/2023
(ይትባረክ ዋለልኝ) የካቲት ወርን የሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ የመታሰቢያ ወር በማለት ላለፉት ሶስት ሳምንት ሲካሄር ቆይቷል::ከየካቲት 4 እስከ የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ በርካታ ዝግጅቶች ቀርበዋል:: በዚህ የሶስት ሳምንት የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የስዕል ስራዎቹ ለእይታ ቀርበዋል:: የማይጠገቡ ግጥሞቹ በታወቁ ጠቢባን ተነበዋል። ስዕሎቹም ከነግጥሞቹ በባለሙያዎች ተተንትነዋል:: ውይይትም ተደርጎባቸዋል:: የህይወት ታሪኩም ቀርቧል:: እንዲሁም ሰለገብረክርስቶስ ደስታ ስራዎች ታላላቅ እንግዶች ከአውሮፓ ከአሜሪካና ከአዲስ አበባ በአካልና በቪድዮ ንግግር አድርገዋል። የመጨረሻው የሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ የመታሰቢያ ወር ነገ ቅዳሜ የካቲት 25 2015 ዓ/ም ከ8:30 ሰዓት ጀምሮ በደመቀ ስነስርዓት በይፋ ይጠናቀቃል::በዚህ ፕሮግራም ላይ - ዐፅሙ ወደሚያፈቅራት ሐገሩ ስለሚመለስበት - የግጥም ስራዎቹና የየካቲት መታሰቢያው አከባበር ስለሚታተምበት እና ተበታትነው ያሉ ስራዎቹ ባንድ ማዕከል ስለሚሰበሰቡበት እና ሙዚየሙ ሙዚየም ስለሚሆንበት ጉዳይ ውይይት ይደረጋል:: በተጨማሪም አጠቃላይ የመታሰቢያው ጭብጦች ሕዝባዊ አቋም ተነቦ ከጎልጎታ ጋር የፎቶግራፍ ስነ ስርዓት ይካሄዳል::በመጨረሻም አዲስና የትም ያልታየ ስለ ገብረክርስቶስ ደስታ የህይወት ታሪክ ዘጋቢ ፊልም ከ11 ሰዓት ጀምሮ ለሕዝብ ይቀርብና የመታሰቢያው ፕሮግራም መደምደሚያ ይሆናል:: ሁላችሁም የዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ተጋብዛችሁዋል !!
test