የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ኬንያ ገብተዋል
Edited by : addiskignit@gmail.com -5/29/2023
የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ኬንያ ገብተዋል። ላቭሮቭ፣ ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። ላቭሮሽ ወደ አፍሪካ በድጋሚ የመጡት፣ የዩክሬኑ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲሚትሮ ኩሌባ በአፍሪካ ጉብኝት ባደረጉ ማግስት ነው። ላቭሮቭ የኬንያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናሉ ተብሏል። ከንግድ ትስስር አንጻር፣ ሩሲያ የኬንያን ሻይ ቅጠል በመግዛት ከዓለም በአምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
test