ታዋቂዋ ድምፃዊት ህብስት ጥሩነህ በቶሮንቶ ለአዲስ ዓመት በዜማ ላውንጅ ሥራዎቿን ታቀርባለች
Edited by : addiskignit@gmail.com -12/29/2022
ህብስት ጥሩነህ በ198ዐዎቹ አጋማሽ በጣፋጭ የልጅነት ድምጿ ወደኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ ስትቀላቀል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዘፈነቻቸውን የብዙነሽ በቀለ የቀድሞ ዘፈኖች ለመስማት ብዙዎች በየቴሌቪዥን መስኮት ፊት ይሰበሰቡ ነበር፡፡ ህብስት በሂደት ወደላቀ የሙያ ደረጃ ራሷን ያሣደገችና በርካታ የካሴትና የሲዲ አልበሞችን ለብቻዋና ከሌሎች ድምፃዊያን ጋር ያቀረበች ተወዳጅ ድምፃዊት ናት፡፡ የፊታችን እሁድ የሚገባውን አዲሱን የፈረንጆች 2ዐ23 ዓመት ለመቀበል በላሊበላ ሬስቶራንት ዌስትና በዜማ ላውንጅ በተዘጋጀው የሶስት ቀናት የሙዚቃ ድግስ ላይ ዋናዋ ድምፃዊት ሆና በቶሮንቶና አካባቢው የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያንና ኤርትራዊያንን ታዝናናለች፡፡ ከዲሴምበር 31 /2ዐ22 እስከ ጃኑዋሪ 1 ቀን 2ዐ23 ድረስ የተዘጋጀውን የአዲስ ዓመት አቀባበል ፓርቲ ከህብስት ጥሩነህ ጋር በዜማ ላውንጅ አሳልፉ ተብላችሁአል ፡፡ መልካም አዲስ ዓመት በቶሮንቶና አካባቢው ለምትኖሩ በሙሉ ተመኝተናል፡፡
test