News

ለአዲስ ቅኝት ቲቪ አንደኛ ዓመት በTAS ህግ ቢሮ ስፖንሰርነት የተካሄደው የሥነ ጽሑፍ ውድድር የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች ታወቁ!

Gezahegn Mekonnen Demissie·
Share
የሥነ ጽሑፍ ውድድር አሸናፊዎች የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች ታወቁ!

የአዲስ ቅኝት ቴሌቭዥን በኦምኒ ስርጭት መጀመር አንደኛ አመትን አስመልክቶ በተክለሚካኤል አበበ ህግ ቢሮ ስፖንሰር በተደረገው የሥነፅሁፍ ውድድር አርባ ገደማ አጫጭርና የአጭር አጭር ታሪኮች እንዲሁም ሌሎች ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ለምርጫው የተመደቡት ዳኞች ከቀረቡት ስራዎች ውስጥ የመረጧቸውንና ለመጨረሻው ዙር ያለፉ ስራዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሠረት ለመጨረሻው ዙር ያለፉ ፀሐፊዎች

1- ፀጋአምላክ ሀይሉ ከአዶላ

2- ሔኖክ ካሳ ከሻሸመኔ

3- ትእግስት በላቸው ከአዲስ አበባ

4- ቃልኪዳን ፈለቀ ከአዳማ ናዝሬት

5- አሸናፊ አይናለም ከአቃቂ ቃሊቲ

6- ፍቃዱ አስራት ከመቂ ሲሆኑ

   ከእነዚህ መካከል ከአንድ እስከ ሶስት የወጡ ተወዳዳሪዎች የተለዩ ሲሆን ውጤቱ በኦገስት 29 ቀን በሚደረገው የአዲስ ቅኝት አንደኛ አመት የቴሌቭዥን ፕሮግራም በአል ላይ ተገልፆ በተክለሚካኤል አበበ ህግ ቢሮ የተዘጋጀላቸው ሽልማት በይፋ ይበረከታል። አንደኛ የወጣው ታሪክም በእለቱ የሚነበብ ሲሆን የገንዘብ ሽልማቱም

አንደኛ ለወጣው የኢትዮጵያ 50 ሺ ብር

ሁለተኛ ለወጣው የኢትዮጵያ 40 ሺ ብር

ሶስተኛ ለወጣው የኢትዮጵያ 30 ሺ ብር ይበረከትላቸዋል።