ለኢትዮጵያ መንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ የአገሪቱ ዓለማቀፍ የልማት አጋሮች ግልጽ ቃል ኪዳን በቡድን-20 ማዕቀፍ ውስጥ የአበዳሪዎች የፋይናንስ ድጋፍ ማረጋገጫ ያስፈልጋል
Edited by : addiskignit@gmail.com -5/12/2023
ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ የአገሪቱ ዓለማቀፍ የልማት አጋሮች ግልጽ ቃል ኪዳን በቡድን-20 ማዕቀፍ ውስጥ የአበዳሪዎች የፋይናንስ ድጋፍ ማረጋገጫ ያስፈልጋል በማለት የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጁሊ ኮዛክ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። ድርጅቱ ለኢትዮጵያ አገር በቀል የኢኮኖሚ መርሃ ግብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ በሚችልበት ኹኔታ ዙሪያ እስካኹንም ከአገሪቱ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር ላይ መኾኑን ቃል አቀባይዋ መጥቀሳቸውን ዜና ምንጩ አመልክቷል። ኢትዮጵያ በቡድን-20 ማዕቀፍ ስር የውጭ ዕዳ ክፍያ ሽግሽግ እንዲደረግላት የጠየቀችው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት 2 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት መጠየቋን ሮይተርስ ባለፈው ወር መዘገቡ ይታወሳል።
test