News

የአዲስ ቅኝት–OMNI ቲቪ የመጀመሪያ ዓመት በዓል በተሳከ ሁኔታ ተከበረ

Gezahegn Mekonnen Demissie·
Share
አዲስ ቅኝት (New Perspective) ስርጭት የጀመረበት የመጀመሪያ ዓመቱን በቶሮንቶ በልዩ ዝግጅት አከበረ።

ቶሮንቶ፦ በካናዳ በOMNI ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የኢትዮጵያ ካናዳውያን ፕሮግራም አዲስ ቅኝት (New Perspective) ስርጭት የጀመረበት የመጀመሪያ ዓመቱን በቶሮንቶ በልዩ ዝግጅት አከበረ።

በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ካናዳዊ ማኅበረሰብ አባላት፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች፣ የቢዝነስ ሰዎች ጸሐፊዎችና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የአንደኛ ዓመት በዓሉ በሙዚቃና መዝናኛ ፕሮግራሞች፣ የፋሽን እና የሜካፕ ትርኢት እንዲሁም የሥነ ጽሑፍ ውድድር ሽልማት ሥነ-ሥርዓትን አካሂዷል። 

በዝግጅቱ ላይ ለወጣት ጋዜጠኞች የተዘጋጀ የጋዜጠኝነት ስኮላርሺፕም ዘንድሮ በቂ ተመዝጋቢ ተማሪ ባለመገኘቱ ሳይካሄድ ቢቀርም ለመጪው ዓመት ተላልፏል!

አዲስ ቅኝት በOMNI ላይ ስርጭቱን ከጀመረ ወዲህ በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያ ካናዳውያንን የሚመለከቱ ዜናዎችን፣ የማኅበረሰብ ጉዳዮችን፣ የሥነ ጥበብና የባህል ዝግጅቶችን እንዲሁም የግለሰቦችን ስኬት የሚያሳዩ ታሪኮችን አቅርቧል።

የፕሮግራሙ የመጀመሪያ ዓመት ስኬት በተለይም የኢትዮጵያ ካናዳዊ ማኅበረሰብ በሜይንስትሪም የካናዳ ሚዲያ ውስጥ የራሱን ድምፅና ታሪክ ለማስተላለፍ ያለውን ፍላጎት የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።

የአዲስ ቅኝት ቡድን በቀጣዩ የስርጭት ዘመንም የማኅበረሰቡን ወቅታዊ ጉዳዮች፣ ባህል፣ ሥነ ጥበብና ስኬቶች ለተመልካቾች ማቅረቡን እንደሚቀጥል ገልጿል።