127ኛው የአድዋ ድል በዓል በቶሮንቶ በድምቀት ተከብሯል
Edited by : addiskignit@gmail.com -3/1/2023
ቶሮንቶ የአድዋ ድልን በዓል ከጥቁሮች የታሪክና የባህል ወር ጋር በተጣጣም መልኩ አክብራለች፡፡ ታዋቂው አፍሪካዊ ካናዳዊ ደራሲ፣ ጋዜጠኛና አክስቲቪስት ዴዝመንድ ኮል በክብር እንግድነትና በዋና ተናጋሪነት በተጋበዘበት በዚሁ የ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በቶሮንቶ ሲከበር በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በነቂስ ወጥተው ባከበሩት በዚሁ በዓል ላይ አድዋ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ድል መሆኑ ተገልጿል፡፡ የትውልድ ሃገሩ ከምእራብ አፋሪካዊቷ ሴራሊዮን የሚመዘዘው ዴዝመን ኮል አድዋ የጥቁር ህዝቦችን ሁሉ ያነቃነቀና በኢምፔሪያሊስቶችና በኮሎኒያሊስቶች ላይ የተገኘ ዘመን አይሽሬ ድል ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን የጥቁር ህዝብ ሁሉ ኩራትና አርአያ ናቸው ሲል ተናግሯል፡፡ በአሉን ያዘጋጀው በቶሮንቶና አካባቢው የኢትዮጵያ ማኀበርና አካባቢው ኘሮዚዳንት ወ/ሮ መሠረት ደመቀ የአድዋን ታሪክ ለልጅ ልጆቻችን የምናወርሰው ቅርሣችን ነው፡፡ በስደት አለም ለምንኖር በሙሉ የክብርና የማንነት መለያችን ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ መድረኩን የመሩት ዶ/ር ዮሃንስ ታደሰ በበኩላቸው አድዋ የአፄ ምንሊክና የእቴጌ ጣይቱ በሣል አመራርና ጦር አዋቂነት የመሠከረበት በቅኝ ገዢዎች ላይ የተገኘ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው ብለዋል፡፡ በእለቱ በተናጋሪነት በአዲስ ቅኝት ሚዲያ የተጋበዘው ጋዜጤኛ ገዛኸኝ መኮንን በበኩል የጥቁሮች መብት ተሟጋቹ ማርክስ ጋርቬይ ወደአፍሪካ መመለስ የሚለውን እንቅስቃሴ የጀመረው በአድዋ ድል ተነሣስቶ ነው ፡፡ ከማርክስ ጋርቬይ እንቅስቃሴ በኋላ በአሜሪካ ፣ በካሪቢያንና በአፍሪካ በባርነትና በቅኝ አገዛዝ ስር የነበሩ ሁሉ በነፃነት ተነሣስተዋል፡፡ አድዋም የድላቸው ሁሉ መነሻ ነበር ሲል ተናግሯል፡፡
test