Ethiopian Airlines Proactively Addresses Passenger Service Concerns at Bole Airport
Edited by : Gezahegn Mekonnen Demissie -3/12/2024
In a proactive move to address rising complaints on social media platforms regarding passenger services at Bole Airport, Ethiopian Airlines steps up its commitment to customer satisfaction. The airline, renowned for its dedication to customer feedback, has initiated a collaborative effort with stakeholders at Addis Ababa Bole Airport to thoroughly investigate and resolve the grievances raised. Assuring swift action, Ethiopian Airlines pledges to implement necessary corrective measures promptly, guided by the outcomes of the investigation. With a steadfast focus on providing efficient and convenient services, Ethiopian Airlines reaffirms its commitment to its esteemed clientele, valuing their feedback and continuously striving for enhancement. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች እየተነሱ መሆኑን ተገንዝቧል። አየር መንገዱ ከክቡራን ደንበኞቹ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ ሂደቱን በጥሞና ሲከታተል ቆይቷል። በመሆኑም እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራት ስራ እየሠራ መሆኑን ለማሣወቅ እንወዳለን። ይህንንም ተከትሎ በማጣራቱ ሥራ ላይ በሚገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት እንዲወሠድ ይደረጋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁልጊዜም ጥረቱ ለውድ ደንበኞቹ ቀልጣፋ እና ምቹ አገልግሎት መስጠት ነው። አሁንም የክቡራን ደንበኞቹን ጥቆማ ተቀብሎ አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ ይህንኑ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
test