የአፍሪካ ኅብረት ሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ቅዳሜ’ለት ባካሄደው ስብሰባ የሱዳኑን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን አስታውቋል
Edited by : addiskignit@gmail.com -5/29/2023
የአፍሪካ ኅብረት ሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ቅዳሜ’ለት ባካሄደው ስብሰባ የሱዳኑን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ፍኖተ ካርታው ካካተታቸው ነጥቦች መካከል፣ ለግጭቱ እየቀረቡ ያሉ ቀጠናዊና ዓለማቀፍ የሰላም ጥረቶችን የሚያስተባብር አንድ ወጥ አካል እንዲቋቋም እና ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች አስቸኳይ፣ ዘላቂና ሁሉን ዓቀፍ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደርሱ ይጠይቃል። ፍኖተ ካርታው፣ የሰላም ጥረቶችን የሚያስተባብረው የተማከለ አካል፣ ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከኢጋድ፣ ከተመድና ዓረብ ሊግ የተውጣጣ እንዲኾን ሃሳብ አቅርቧል።
test