አንጋፋዋና ዝነኛዋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ በ83 ዓመቷ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
Edited by : addiskignit@gmail.com -5/12/2023
አንጋፋዋና ዝነኛዋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ በ83 ዓመቷ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየች የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኂሩት ከ1953 ዓ፣ም ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኖችን የተጫወተች ተወዳጅ ድምጻዊት ነበረች። ድምጻዊት ኂሩት ወደ መጨረሻው የሕይወት ዘመኗ ገደማ ዓለማዊ ሙዚቃዎችን መዝፈን አቁማ፣ ሐይማኖታዊ መዝሙሮችን ስትዘምር እንደነበር ይታወቃል። ዋዜማ ለአንጋፋዋ ድምጻዊት ኂሩት ቤተሰቦችና ለአድናቂዎቿ መጽናናትን ትመኛለች።
test