የግል ባንኮች በአሁኑ ወቅት ለአንድ ዶላር የሚያስከፍሉት ኮሚሽን ወደ 65 ብር ማደጉ ተሰምቷል
Edited by : addiskignit@gmail.com -3/3/2023
የግል ባንኮች በአሁኑ ወቅት ለአንድ ዶላር የሚያስከፍሉት ኮሚሽን ወደ 65 ብር ማደጉ ተሰምቷል። የአንድ የአሜሪካ ዶላር የባንኮች መሸጫ ዋጋም ከ110 ብር ወደ 115 ብር ጨምሯል። የውጭ ምንዛሬ ግብይቱ የሚፈጸመው፣ በባንክ የውጭ ምንዛሬ ባስቀመጡ ግለሰቦችና በውጭ ምንዛሬ ፈላጊዎች መካከል በደላሎች አገናኝነት ነው። አስመጪዎች አገር ውስጥ በብር ክፍያ ፈጽመው ውጭ አገር ባሉ ሰዎች ለሚፈልጉት ዕቃ በውጭ ምንዛሬ ክፍያ ተፈጽሞላቸው ዕቃ ለማስገባትም፣ ለአንድ ዶላር በተመሳሳይ 105 ብር ይከፍላሉ። ባንኮች የሚሸጡት የውጭ ምንዛሬም ከጥቁር ገበያው ጋር ተመሳሳይ እየሆነ መምጣቱ ታውቋል። ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ለአንድ ዶላር መሸጫ ያወጣው ዋጋ ግን፣ 54 ብር ከ83 ሳንቲም ነው።
test